ቦረን (የሙርቲ ጸሎት ጥሪ) - ከሎሬት ፀጋዬ ገበረመድህን ቀዌሳ

borana-blessing
borana
ቦረን-የሙርቲ
oromo-blessing
blessing-in-court

#1

ቦረን (የሙርቲ ጸሎት ጥሪ)

፡ ሃይ ሃይ
ጸጥታ ይሁን …
አንት የሠራህ ሁሉን
አምላክ ጋዳን ባርክ፥
ሃሳብን አጥና
ፈረስን አቅና
እምቦሳን አጥባ
ጊደሩን አርባ
ኮርማውን አስባ
ምድሪቱን አጽድቅ
ጠላትን አድቅቅ
ዝሆን-ጎሽ አድቅቅ
ጦርን አቅናልን
ግዳይ ጣልልን
ምርኮን አግባልን
ማርዳውን አጥልል
ጸጋን ለኛ አክል
ሥርዓቶን አውል
በዐሉን ዐድል
በዐሉን ዐድል…
ቀጥል፤
፡ ሃይ ሃይ፥
ጸጥታ ይሁን…
-ለማዳ ጋልማ አባ ጋዳ / ዲሬ