ምነው አምቦ? ከሎሬት ፀጋዬ ገበረመድህን ቀዌሳ

tsegaye-gebremedhin
ፀጋዬ-ገበረመድህን

#1

ምነው አምቦ?

image

ምነው አምቦ …
የደማም አምባዎች ቁንጮ ፥ እንዳልነበርሽ የደም ገንቦ
እንዳልነበርሽ ንጥረዘቦ
ዙሪያሽ በምንጭ ታጅቦ
በተራሮችሽ ትከብቦ
ከጠበልሽ ሢሳይ ታልቦ
ከአዝርእትሽ ፍሬ ዘንቦ
ከዓመት ዓመት ጤና አብቦ
ሕይወት ደርቶ ሰላም ቀርቦ …
የአየር ትፍሥሕት እንዳልነበርሽ፥ የዘር ሆነ የእሸት የአትክልት
ከመጫ እስከ አዋሽ እምብርት
ምንጭሽ ሲያጥጥ ሲፍለቀለቅ፥ ከዳንዲ እስከ ዋንጪ እትብት …
እንዳልነበርሽ የምድር አድባር፥ የዘር ድባብ ያገር ችቦ
ዛሬ እንደዚህ ምነው አምቦ
የቀትር ጥላሽ ተስቦ
የጡቶችሽ ወዝ ተሰልቦ
የመዓዛሽ መፍለቅለቂያ፥ መንጸብርቅሽ ተሸብቦ
ተረምርሞ ተተብትቦ …
ምነው፧ … ምነው አምቦ?