ገዳ - By Hiriya Dhufera


#1

ገዳ
ገዳ ቛንቛ ገዳ እውነት
ገዳ ታሪክ ኪዳን እምነት
ገዳ ትግል ነፃ መውጫ
ድልድይ ብስራት መወጣጫ
ህብር መዝሙር ማሸነፍያ
ቃል ማሰርያ መሰለፍያ
ገዳ ይቅርታ ገዳ ፀሎት
መለመኛ መታረቅያ ማን ከልክሎት
እኩል መሆን ፍትህ ማግኛ
ዲሞክራሲ መገናኛ
ገዳ አስተዋይ ፍርድ አዋቂ
በዳይ አጥፊን ገሀድ ጠያቂ
ገዳ ወጣት ክንደ ብርቱ
ሽማግሌ እድሜ ጠገብ ርዕቱ
የበኩር ልጅ ነገደ ኩሽ
የኑብያ ቅርስ ግማሽ
ኤሬቻ የገዳ ቁራሽ
ገዳ ጠዋት ጀንበር መራሽ
ፍንጥቅጣቂ ድምቀት አጉራሽ
የገዳ አካል ኤሬ ግማጅ
የደም አጥንት አንድ ጥማጅ
ገዳ መንገድ መሪ አራማጅ
ፊት ቀዳሚ ገዳ ፈራጅ
ገዳ ኦዳ መጠለያ
ማደርያ ቤት መገልገያ
ድብቅ ሚስጥር ያልተፈታ
ገሀድ የሚታይ ግልፅ እውነታ
አልፋ ኦሜጋ
ገዳ ኤጋ
ገዳ eegaa !!!
By Hiriya Dhufera